ስለ AppGallery እና ግላዊነት መግለጫ
መጨረሻ የታደሰው፦ ጃንዋሪ፣ 2020
AppGallery ሆንግ ኮንግ ውስጥ በተደራጀው የHuawei እህት ኩባንያ በሆነው Huawei Services (Hong Kong) Co., Limited, (ከአሁን በኋላ "እኛ"፣ "በእኛ"፣ ወይም "የእኛ" ተብሎ በሚጠራ) የሚቀርብ አገልግሎት ነው። ነጻ እና የሚከፈልባቸው መተግበሪያዎችን ማሰስ፣ መድረስ፣ ማውረድ እና ማስተዳደር የሚችሉበት የማከፋፈያ ስርዓተ መድረክን ለእርስዎ ያቀርባል።
ይህ መግለጫ የሚከተሉትን ይገልጻል፦
1. ስለ እርስዎ የምንሰበስበው ውሂብ ምንድን ነው?
2. ውሂብዎን የምንጠቀመው እንዴት ነው?
3. ውሂብዎን የምናስቀምጠው ለምን ያህል ጊዜ ነው?
4. ውሂብዎን የምናጋራው እንዴት ነው?
5. የእርስዎ መብቶች እና አማራጮች ምንድን ናቸው?
6. እኛን እንዴት ነው ማግኘት የሚችሉት?
7. ይህን መግለጫ የምናድሰው እንዴት ነው?
1. ስለ እርስዎ የምንሰበስበው ውሂብ ምንድን ነው?
እንደ የAppGallery አገልግሎት አካል የግል ውሂብዎን የምንሰበስበውና የምንጠቀመው በዚህ መግለጫ ውስጥ ለተገለጹት ዓላማዎች ብቻ ነው። የግል ውሂብ ማለት እኛ እርስዎን እንደ አንድ ተጠቃሚ ለይተን እንድናውቀዎት የሚያስችለን ማንኛውም መረጃ ማለት ነው።
የሚከተለውን ውሂብ ሰብስበን እናሰናዳለን፦
•የHUAWEI መታወቂያ መለያ መረጃ፣ ለምሳሌ እንደ የመለያ ስም (ኢሜይል ወይም የስልክ ቁጥር)፣ የመገለጫ ምስል፣ ቅጽል ስም፣ የትውልድ ቀን፣ የሀገር/ክልል ኮድ፣ የመለያ ለዪ፣ እና የመለያ ለዪ አገልግሎት ቶከን።
•የመሳሪያ መረጃ፣ ለምሳሌ የመሳሪያ ለዪ (በመሳሪያዎ የስርዓት ስሪት የሚወሰን ሆኖ እንደ SN፣ UDID ወይም IMEI ያሉ)፣ የቋንቋ ቅንብሮች፣ የመሳሪያ ሞዴል፣ የመሳሪያ ስርዓተ ክወና ስሪት እና የሮም ስሪት፣ የማያ ትልቀት እና የምስል ጥራት፣ የሞባይል ሀገር ኮድ፣ የማድረሻ ሀገር።
•የአውታረ መረብ መረጃ፣ ለምሳሌ እንደ የIP አድራሻ፣ የአውታረ መረብ አይነት፣ እና የአውታረ መረብ ግንኙነት ሁኔታ ያሉ።
•የአገልግሎት አጠቃቀም መረጃ፣ ለምሳሌ የAppGallery ስሪት ቁጥር እና የማውረጃ ምንጭ፣ የመተግበሪያ አጠቃቀም ቆይታ ጊዜ፣ የመተግበሪያ ጠቅታ እና ተጋላጭነት ጊዜያት፣ የመተግበሪያ ፍለጋ ታሪክ፣ መተግበሪያ የማውረድ እና የመጫን ታሪክ እና ውጤቶች፣ የመተግበሪያ በመለያ መግባት ውጤቶች፣ የተጫኑ መተግበሪያዎች መረጃ (ለምሳሌ ምድቦች እና ስሪት)፣ የተራገፉ መተግበሪያዎች ዝርዝር፣ የመተግበሪያ ግዢ ትዕዛዝ መጠን፣ የታዘዘበት ጊዜ፣ የትዕዛዝ መታወቂያ፣ የተጠቃሚ ሽልማት (ስጦታዎች) መዝገብ፣ የመተግበሪያ አስተያየቶች፣ የተጠቃሚ ስምምነት ፊርማ መዝገብ፣ የመተግበሪያ ማስተዋወቂያ ሰርጥ መታወቂያ፣ የመተግበሪያ ድህረ ገጽ መገናኛ፣ እና የምኞት ዝርዝር መተግበሪያዎች።
•የጨዋታ አገልግሎቶች መረጃ፣ ለምሳሌ እየተጫወቱ ካሉት የጨዋታ መተግበሪያ አቅራቢ የምንቀበላቸው የተጫዋች መታወቂያ፣ ደረጃዎች፣ ስኬቶች፣ የተጫዋች ስታቲስቲኮች፣ እና የጨዋታ አጠቃቀም ውሂብ።
በHUAWEI AppGallery ማስተዋወቂያዎች ጊዜ በአንዱ ላይ ሽልማት ካሸነፉ፣ የእርስዎ የመላኪያ አድራሻ እና የስልክ ቁጥር/ኢሜይል አድራሻ ሽልማቱን ለእርስዎ ለማድረስ ይሰናዳሉ።
በጎብኚ ሁነታ ላይ ሆነው (በHuawei መታወቂያ መለያዎ ሳይገቡ) HUAWEI AppGalleryን ከተጠቀሙ የሚከተለው ውሂብ ይሰበሰብና ይሰናዳል፦
•የመሳሪያ መረጃ፣ ለምሳሌ የመሳሪያ ለዪ በመሳሪያዎ የስርዓት ስሪት የሚወሰን ሆኖ እንደ SN፣ UDID ወይም IMEI ያሉ፣ የቋንቋ ቅንብሮች፣ የመሳሪያ አይነት፣ የመሳሪያ ስርዓተ ክወና ስሪት እና የሮም ስሪት፣ የማያ ትልቀት እና የምስል ጥራት፣ የመላኪያ ሀገር።
•የአውታረ መረብ መረጃ፣ ለምሳሌ እንደ የIP አድራሻ፣ የሞባይል ሀገር ኮድ (MCC)፣ የሞባይል አውታረ መረብ ኮድ (MNC)፣ የአውታረ መረብ አይነት እና የአውታረ መረብ ግንኙነት ሁኔታ።
•የአገልግሎት አጠቃቀም መረጃ፣ ለምሳሌ እንደ የAppGallery ስሪት ቁጥር፣ መተግበሪያ የተከፈተበት እና የተዘጋበት ጊዜ፣ ጠቅታዎች፣ ተጋላጭነት፣ የመተግበሪያ ፍለጋ ታሪክ፣ መተግበሪያ የማውረድ እና የመጫን ታሪክ፣ የተጫኑ መተግበሪያዎች መረጃ (ለምሳሌ ምድቦች እና ስሪት)፣ የተጫኑ መተግበሪያዎች ዝርዝር፣ የክወና መዝገቦች እና የስህተት መዝገቦች፣ የመተግበሪያ ማስተዋወቂያ ሰርጥ መታወቂያ፣ የመተግበሪያ ድህረ ገጽ መገናኛ፣ እና የተጠቃሚ ስምምነት ፊርማ መዝገብ።
አስፈላጊዎቹን አገልግሎቶችን ለእርስዎ ለማቅረብ AppGallery የመሳሪያዎን መረጃ ለማግኘት ስልክዎን የመድረስ፣ እና የመጫኛ ፓኬጆችን ለማስተዳደር ማከማቻዎን የመድረስ ፈቃዶች ያስፈልጉታል። ፈቃዶችን እንዲሁም በመሳሪያዎ ቅንብሮች ውስጥ ማስተዳደር ይችላሉ።
2. ውሂብዎን የምንጠቀመው እንዴት ነው?
የAppGallery አገልግሎቶችን ለእርስዎ ለማቅረብ እና የውል ግዴታዎችን ለሟሟላት፣ የግል ውሂብዎን እርስዎ መተግበሪያዎችዎን ማሰስ፣ መድረስ፣ ማውረድ፣ ማስተዳደር እንዲችሉ፣ እና ከጨዋታ ጋር በተያያዙ ባህሪያት እንዲዝናኑ መሰብሰብ ያስፈልገናል። ይህ እንዲሁም ማንነትን ለመለየት፣ አለመግባባትን ለመፍታት፣ ለደንበኛ ግንኙነት አስተዳደር፣ ለድጋፍ እና ግንኙነት፣ ለደንበኛ ቅሬታ አያያዝ፣ ለጥገና፣ ለስርዓት ማዘመኛዎች፣ ለችግር ምርመራ እና ጥገና ውሂብዎን እንድናሰናዳ ያስችለናል።
በተጨማሪም፣ የግል ውሂብዎን በእርስዎ ፈቃድ ለሚከተሉት አላማዎች እንጠቀማለን፦
•ለትንታኔ እና ማስፋፊያ አላማዎች፣ በተለያዩ የተጠቃሚ ቡድኖች የአጠቃቀም እንቅስቃሴ ላይ በመመስረት የተጠቃለሉ ቡድኖችን መፍጠርን ጨምሮ። ይህ እንዲሁም ተጠቃሚዎቻችን እንደ ደንበኞች ያላቸውን ፍላጎቶች እንድንረዳ እና የእኛን የአሁን እና የወደፊት አገልግሎቶች እና አቅርቦቶች ጥራት እና የተጠቃሚ ተሞክሮ እንድናሻሽል፣ እንዲሁም የዘመቻዎችን እና የማስተዋወቂያዎችን ውጤታማነት እንድንገመግም ያስችለናል። ከታች በአንቀጽ 5.6 ላይ እንደተገለጸው እንደዚህ ያለውን የውሂብ መሰናዳት መቃወም ይችላሉ።
•ስለ እኛ አቅርቦት፣ የሽያጭ ማስተዋወቂያ እና የገበያ ስራ ዓላማዎች ለመነጋገር እና እንዲሁም የተጠቃለሉ ዒላማ ቡድኖችን ለገበያ ስራ ለመፍጠር ጨምሮ። የደንበኞችን ምርጫዎች ማወቅ አቅርቦታችንን እንድናነጣጥር እና የደንበኞቻችንን ፍላጎቶች እና ምኞቶች በተሻለ የሚያሟሉ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን እንድናቀርብ ያስችለናል። ከታች በአንቀጽ 5.6 ላይ እንደተገለጸው እንደዚህ ያለውን የውሂብ መሰናዳት መቃወም ይችላሉ።
•AppGallery ውስጥ ምክሮችን በማቅረብ እና የተነጣጠሩ መተግበሪያዎችን በማሳየት አገልግሎቶችን ግላዊነት የተላበሱ ለማድረግ የግል ውሂብዎን ልናሰናዳ እንችላለን። ከታች በአንቀጽ 5.6 ላይ እንደተገለጸው እንደዚህ ያለውን የውሂብ መሰናዳት መቃወም ይችላሉ።
•በመሳሪያዎ ላይ HUAWEI ማስታወቂያዎችን ግላዊነት ማላበስ ስራ ካስጀመሩ፣ የተጫኑ መተግበሪያዎችዎ ምድቦች (ለምሳሌ ጨዋታዎች፣ ማህበራዊ ሚዲያ፣ ስፖርቶች) በHuawei Mobile Services እና በሦስተኛ ወገን መተግበሪያዎች ላይ ተጨማሪ የሚስማሙ ማስታወቂያዎችን በHUAWEI ማስታወቂያዎች ስርዓተ መድረክ ለእርስዎ ለማቅረብ ጥቅም ላይ ይውላሉ። ስለ Huawei ማስታወቂያዎች እና ስለ እርስዎ መብቶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ (https://consumer.huawei.com/ minisite/cloudservice/ad /privacy-statement.htm?country=HK&language=am-et) ላይ ጠቅ ያድርጉ።
•ለመረጃ ደህንነት ዓላማዎች፥ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና አስተማማኝ አገልግሎቶችን ለእርስዎ ለማቅረብ የተለያዩ ዓይነት አገልግሎቶችን ያለአግባብ መጠቀም እና ማታለሎችን አጣርቶ ማግኘት ወይም መከላከል ጨምሮ።
•በሶስተኛ ወገን የጨዋታ መተግበሪያ ውስጥ የጨዋታ አገልግሎቶችን ስራ ካስጀመሩ፣ እና መተግበሪያው የእርስዎን የጨዋታ አገልግሎቶች ውሂብ (የተጫዋች መታወቂያ፣ ደረጃዎች፣ ስኬቶች፣ እና የተጫዋች ስታቲስቲኮች) እንዲያገኝ ከፈቀዱ፣ የእርስዎ የጨዋታ አገልግሎቶች ውሂብ ለሶስተኛ ወገኑ የጨዋታ መተግበሪያ ይፋ ይደረጋል። እንደዚህ ያሉ ፈቀዳዎችን በመሳሪያዎ ላይ በማንኛውም ጊዜ ወደ ቅንብሮች > HUAWEI መታወቂያ > የግላዊነት ማዕከል > የመለያ መዳረሻን ይቆጣጠሩ በመሄድ መሻር ይችላሉ።
•AppGallery ውስጥ የሚገኝ መተግበሪያ ላይ አስተያየት ከሰጡ፣ የመተግበሪያው አበልጻጊ በእርስዎ ግብረመልስ እና ደረጃ አሰጣጥ ላይ በመመስረት አገልግሎቱን እንዲያሻሽሉ ለመርዳት የእርስዎን አስተያየት እና ቅጽል ስም ይፋ እናደርግላቸዋለን።
በHUAWEI መታወቂያዎ ገብተው HUAWEI AppGalleryን ሲጠቀሙ፣ AppGallery መተግበሪያው ውስጥ ፍቃድዎን ከሰጡ በኋላ፣ ስለሚገኙ አዲስ መተግበሪያዎች፣ ክስተቶች፣ እና ከስጦታ ጋር ስለሚገናኙ እንቅስቃሴዎች እርስዎን ለማሳወቅ ተገፊ ማሳወቂያዎችን ወደ መሳሪያዎ ልንልክ እንችላለን። በማንኛውም ጊዜ ወደ AppGallery > የእኔ > ቅንብሮች በመሄድና ማሳወቂያዎችን ስራ በማስቆም የሰጡትን ፈቃድ መሻር ይችላሉ።
እንዲሁም የእርስዎን የመተግበሪያ ግዢ ትዕዛዝ መጠን፣ የታዘዘበት ጊዜ እና የትዕዛዝ መታወቂያን እኛን በሚመለከቱ ህጎች እና ደንቦች እንደተፈለገው ለግብር እና ለሒሳብ ስራ ዓላማዎች ልናሰናዳ እንችላለን።
3. ውሂብዎን የምናስቀምጠው ለምን ያህል ጊዜ ነው?
የግል ውሂብዎን የምናስቀምጠው በዚህ መግለጫ ውስጥ ለተገለጹት ዓላማዎች አስፈላጊ እስከሆነበት ጊዜ ድረስ ብቻ ነው።
የእርስዎን ውሂብ ከእኛ ጋር ባለዎት የደንበኛ ግንኙነት ቆይታ ጊዜ ውስጥ እናሰናዳለን እና እናስቀምጣለን። የHUAWEI መታወቂያዎን መለያ ከሰረዙ፣ ከመለያዎ ጋር የተዛመዱ ሁሉም የግል ውሂብ እና አገልግሎቶች፣ AppGallery መተግበሪያን ጨምሮ፣ ይደመሰሳሉ። ይሁንና፣ የሚከተሉትን ለተገለጹት ጊዜያት እናቆያለን፦
•የመተግበሪያ ግዢ ትዕዛዝ መጠን፣ የታዘዘበት ጊዜን፣ እና የትዕዛዝ መታወቂያን ክፍያው ከተፈጸመበት አንስቶ ለሰባት (7) ዓመታት።
•ለደንበኛ ግንኙነት አስተዳደር የተሰናዳ የግል ውሂብ፣ ለምሳሌ የውሂብ ጉዳይ ጥያቄዎች፣ ቅሬታዎች፣ እና የደንበኛ መስተጋብር መዝገቦች ከመጨረሻው መስተጋብር አንስቶ እስከ ስድስት (6) ዓመታት።
•ለውል አስተዳደር ዓላማዎች የተሰናዳ የግል ውሂብን የHUAWEI መታወቂያዎ ከተሰረዘ በኋላ እስከ ሶስት (3) ዓመታት ድረስ።
•ለስታቲስቲካዊ ትንታኔ እና ለምርት ማስፋፊያ፣ እንዲሁም ለሽያጭ ማስተዋወቂያ እና ለገበያ ስራ ዓላማዎች የተሰናዳ የግል ውሂብን ከተሰበሰበበት ቀን አንስቶ እስከ አስራ ሁለት (12) ወራት፣ እንደዚህ ያለ ማሰናዳትን ከተቃወሙ በስተቀር።
•የእርስዎን አድራሻ እና የስልክ ቁጥር/ኢሜይል አድራሻ፣ ሽልማቱ ለእርስዎ ከተላከ በኋላ ለአንድ (1) ዓመት።
•የእርስዎን ውሂብ እና አገልግሎቶች ደህንነት ለማረጋገጥ የሚሰናዱ የውሂብ ምትኬዎች እና የመተግበሪያ መዝገቦች፣ ከተፈጠሩበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስት (6) ወራት።
•የጨዋታ አገልግሎቶችን ስራ ካስቆሙ፣ ከላይ እንደተገለጸው ውሂብዎን ማሰናዳት የሚያስቀጥሉ ህጋዊ መሰረቶች ካሉ በስተቀር ውሂብዎ በሰላሳ (30) ቀናት ውስጥ ይወገዳል። አገልግሎቱን በጎብኚ ሁነታ ሆነው በሚጠቀሙበት ጊዜ የእርስዎ የአውታረ መረብ መረጃ እና የአጠቃቀም መረጃ ለሰባት (7 ) ቀናት ይሰናዳል።
አንዴ የማቆያ ጊዜው ካበቃ በኋላ በሚመለከታቸው ህጎችና ደንቦች ከተጠየቀ በስተቀር የእርስዎን የግል ውሂብ እንሰርዘዋለን ወይም ማንነት እንዳይገልጽ እናደርገዋለን።
4. ውሂብዎን የምናጋራው እንዴት ነው?
ውሂብዎን ሆንግ ኮንግ (ቻይና) እና ሲንጋፖር በሚገኙ የውሂብ ማዕከሎች ላይ እናከማቻለን።
የእኛ የጥገና ክወናዎች ውሂብዎን ከህንድ እና ከቻይና እንድንደርስበት ሊፈልጉብን ይችላል። በተጨማሪም፣ በሚኖሩበት አካባቢ የሚወሰን ሆኖ የእርስዎ ውሂብ በሌሎች ሀገሮች ለምሳሌ፣ ሜክሲኮ፣ ግብጽ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሳኡዲ አረቢያ፣ ፓኪስታን፣ ሚያንማር፣ ህንድ እና ማሌዥያ በሚገኙ አካባቢያዊ የደንበኛ አያያዝ ማዕከሎቻችን ሊሰናዳ ይችላል።
የእርስዎን ውሂብ የምናጋራው፦
•AppGallery ውስጥ የሚገኝ መተግበሪያ ላይ አስተያየት ሲሰጡ፣ የእርስዎ አስተያየት፣ ቅጽል ስም፣ የመሳሪያ ሞዴል እና አስተያያት የተሰጠበት ጊዜ አገልግሎትን ለማሻሻል እና/ወይም ችግሮችን ለማስተካከል ለመተግበሪያው አበልጻጊ ይፋ ይደረጋሉ።
•የጨዋታ አገልግሎቶችን ስራ ሲያስጀምሩ እና የሶስተኛ ወገን የጨዋታ መተግበሪያ የእርስዎን የጨዋታ አገልግሎቶች ውሂብ እንዲያሰናዳ ፍቃድ ሲሰጡ፣ የእርስዎ የተጫዋች መታወቂያ፣ ደረጃዎች፣ ስኬቶች፣ ግዢዎች፣ እና የተጫዋች ስታቲስቲኮች ለእርስዎ የጨዋታ ባህሪያትን ለማቅረብ እና የጨዋታ ተሞክሮዎን ለማሻሻል ለሶስተኛ ወገኑ የጨዋታ መተግበሪያ ይፋ ይደረጋሉ።
•የእርስዎን የጨዋታ አገልግሎቶች ውሂብ በእርስዎ Cloud ላይ ለማስቀመጥ ሲመርጡ፣ እና AppGallery ውስጥ የአገልግሎት ሀገር/ክልልን ሲቀይሩ፣ ያስቀመጡት የጨዋታ-ውስጥ ውሂብ ለእርስዎ የCloud አገልግሎቶችን ለሚያቀርቡ እና በእርስዎ የHUAWEI መታወቂያ ምዝገባ ሀገር/ክልል የሚወሰን ሆኖ ቻይና ወይም አየርላንድ (https://cloud.huawei.com/privacyStatementTransit) ለሚገኙ ሌሎች የHuawei እህት ኩባንያዎች ይፋ ይደረጋል።
•በሚመለከታቸው ህጎች ወይም ከህጋዊ ሂደት ጋር በተያያዘ ለህጋዊ ሂደት ወይም ከሚመለከተው ባለስልጣን ለሚመጣ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ሲያስፈልግ።
•እንደ ውህደት፣ የውርስ፣ የንብረቶች ሽያጭ (እንደ የአገልግሎት ስምምነቶች ያሉ) ወይም እንደ የአገልግሎት ወደ የHuawei ቡድን አካል ወይም ወደ ሌላ ኩባንያ የመሸጋገር አካል ሆኖ ሲያስፈልግ።
5. የእርስዎ መብቶች እና አማራጮች ምንድን ናቸው?
የሚከተሉት መብቶች እና አማራጮች አሉዎት፦
5.1 ውሂብዎን መድረስ
መሳሪያዎ ላይ ወደ ቅንብሮች > HUAWEI መታወቂያ > የግላዊነት ማዕከል > ውሂብዎን ይጠይቁ በመሄድ ከAppGallery ጋር በተያያዘ ሰብስበን ያስቀመጥነው የግል ውሂብዎን ቅጂ እና መግለጫ መጠየቅ ይችላሉ።
ለተጨማሪ የመዳረሻ ጥያቄ፣ በጎብኚ ሁነታ ውስጥ ሆነው AppGalleryን ሲጠቀሙ የውሂብዎን ቅጂ መጠየቅን ጨምሮ፣ እባክዎ ያነጋግሩን (https://consumer.huawei.com/ uk/legal/privacy-questions)።
5.2 ውሂብዎን ማስተካከል
ውሂብዎ ወቅቱን የጠበቀ እና ትክክለኛ እንደሆነ ለማቆየት፣ ወደ ቅንብሮች > HUAWEI መታወቂያ በመሄድ ውሂብዎን መድረስ እና ማስተካከል ይችላሉ።
ወደ AppGallery > የእኔ > ቅንብሮች > የመላኪያ መረጃ በመሄድ የእርስዎን የመላኪያ መረጃ መድረስ እና ማስተካከል ይችላሉ።
5.3 ውሂብዎን ማዛወር
መሳሪያዎ ላይ ወደ ቅንብሮች > HUAWEI መታወቂያ > የግላዊነት ማዕከል > ውሂብዎን ይጠይቁ በመሄድ ከAppGallery ጋር በተያያዘ ለእኛ ያቀረቡትን የግል ውሂብ በተለምዶ ስራ ላይ በሚውል እና በማሽን ሊነበብ ወደሚችል ቅርጸት ማዛወር ይችላሉ።
እንዲሁም አገልግሎቱን በጎብኚ ሁነታ ላይ ሆነው በሚጠቀሙበት ጊዜ AppGallery ውስጥ ለእኛ የሰጡትን የግል ውሂብ እኛን በማነጋገር በተለምዶ ስራ ላይ በሚውል እና በማሽን ሊነበብ ወደሚችል ቅርጸት ማዛወር ይችላሉ።
5.4 ውሂብዎን መደምሰስ
እርስዎ በማንኛውም ጊዜ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦
•ወደ AppGallery > የእኔ > የግዢ ታሪክ በመሄድ የእርስዎን የመተግበሪያ ማውረድ እና መጫን ታሪክ እና የግዢ መዝገቦች መሰረዝ።
•ወደ AppGallery > የእኔ > ስጦታዎች በመሄድ የእርስዎን የስጦታዎች መዝገቦች መሰረዝ።
•ወደ AppGallery > የእኔ > የምኞት ዝርዝር በመሄድ የምኞት ዝርዝር ውስጥ ያሉ መተግበሪያዎችን መሰረዝ።
•ወደ AppGallery > የእኔ > ቅንብሮች > የመላኪያ መረጃ በመሄድ የእርስዎን የመላኪያ መረጃ መሰረዝ።
•የHUAWEI መታወቂያ መለያዎን መሰረዝ። በዚህም ምክንያት፣ ከHUAWEI መታወቂያዎ ጋር የተዛመዱ ሁሉም የግል ውሂብ እና አገልግሎቶች፣ AppGallery ውስጥ ያለ የግል ውሂብዎን ጨምሮ ይደመሰሳሉ።
•በአንቀጽ 5.6 ውስጥ እንደተገለጸው የውሂብዎን መሰናዳት መቃወም። ተቃውሞዎ ትክክለኛ ከሆነ እና ውሂብዎን ማሰናዳቱን ለመቀጠል ሕጋዊ መሰረት የሌለን ከሆነ በእርስዎ ተፈጻሚ ተቃውሞ ወሰን ውስጥ የሚወድቀውን የሚመለከተውን ውሂብ እንደመስሳለን።
•የግል ውሂብዎ መሰናዳት ህገወጥ እንደሆነ እና ውሂብዎ መደምሰስ እንዳለበት ካሰቡ ያነጋግሩን (https://consumer.huawei.com/ uk/legal/privacy-questions)።
የግል ውሂብዎን ቀድመው በተገለጹት ድርጊቶችዎ ላይ በመመስረት እና አንቀጽ 3 ውስጥ በተገለጹት የማቆያ ጊዜዎች ላይ በመመስረት ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ እንደመስሰዋለን ወይም ማንነት የማያሳውቅ እናደርገዋለን።
5.5 የሰጡትን ፈቃድ መሻር
ከእኛ ኤሌክትሮኒካዊ ቀጥተኛ የገበያ ስራን መቀበል ለማቆም ከመረጡ፣ በመሳሪያዎ ላይ ወደ AppGallery > የእኔ > ቅንብሮች በመሄድ እና ማሳወቂያዎች ተቀበልን ስራ በማስቆም የሰጡትን ፈቃድ መሻር ይችላሉ።
የሶስተኛ ወገን የጨዋታ መተግበሪያዎች የእርስዎን የጨዋታ አገልግሎቶች መረጃ እንዲቀበሉ ፍቃድ ከሰጡ፣ ወደ ቅንብሮች > HUAWEI መታወቂያ > የግላዊነት ማዕከል > የመለያ መዳረሻን ይቆጣጠሩ በመሄድ የሰጡትን ፈቃድ መሻር ይችላሉ።
5.6 ማሰናዳትን መቃወም
የእርስዎ ውሂብ ለትንታኔ፣ ለምክሮች፣ ለማስፋፊያ ወይም ለሽያጭ እና ለገበያ ስራ አላማዎች መሰናዳቱን መቃወም ከፈለጉ፣ እባክዎን ያነጋግሩን (https://consumer.huawei.com/ uk/legal/privacy-questions)።
ጥያቄውን ሲያቀርቡ እባክዎ የጥያቄውን ወሰን ይግለጹ እና አገልግሎቱን የተጠቀሙት በመለያ ገብተው ከሆነ፣ ወደ HUAWEI መታወቂያዎ ለመግባት የተጠቀሙትን ኢሜይል አድራሻዎን ወይም የስልክ ቁጥርዎን ይስጡን፣ ወይም ደግሞ AppGalleryን በጎብኚ ሁነታ ሲጠቀሙ ከነበረ የመሳሪያ ለዪዎን ይስጡን።
ባቀረቡት ጥያቄ ለመቀጠል የእርስዎን ማንነት ለማረጋገጥ እናነጋግረዎታለን።
5.7 ማሰናዳትን መገደብ
የግል ውሂብዎን ማሰናዳት ለመገደብ ከፈለጉ እባክዎ ያነጋግሩን (https://consumer.huawei.com/ uk/legal/privacy-questions)። እርስዎ በሚከተሉት ሁኔታዎች ስር የውሂብዎን መሰናዳት የመገደብ መብት አለዎት፦
•ውሂብዎ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ሲሰናዳ፣ ነገር ግን መደምሰስ ካልፈለጉ።
•ሊመሰርቱት፣ ሊጠቀሙት፣ ወይም ሊከላከሉት የሚያስፈልግዎት እና ውሂብዎን ሳንጠብቅ ስንቀር እንድንጠብቀው ሊጠይቁን የሚችሉት ህጋዊ የይገባኛል ጥያቄ ሲኖርዎት።
•የግል ውሂብዎን ትክክለኛነት ተጠራጥረው ተቃውሞ ሲያስገቡ እናም የውሂብዎ ትክክለኛነት በእኛ መረጋገጥን በመጠባበቅ ላይ ሲሆን።
•የተቃውሞ ጥያቄዎ በእኛ መረጋገጥን በመጠባበቅ ላይ ሲሆን።
ጥያቄውን ሲያቀርቡ እባክዎ የጥያቄውን ወሰን እና መሰረት ይግለጹ፣ እና ወደ እርስዎ የHUAWEI መታወቂያ ለመግባት የሚጠቀሙበትን የእርስዎን ኢሜይል አድራሻ ወይም የስልክ ቁጥር ይስጡን።
ባቀረቡት ጥያቄ ለመቀጠል የእርስዎን ማንነት ለማረጋገጥ እናነጋግረዎታለን።
6. እኛን እንዴት ነው ማግኘት የሚችሉት?
የውሂብ ጉዳይ መብቶችዎን እንዴት እንደሚጠቀሙ ለማወቅ አንቀጽ 5 ውስጥ መመሪያ ማግኘት ይችላሉ። እንደ የውሂብ ጉዳይ የእርስዎ መብቶች ላይ ወይም የግል ውሂብዎ በእኛ መሰናዳቱ ላይ ማናቸውም ጥያቄዎች፣ አስተያየቶች፣ ወይም ምክረ ሀሳቦች ያለዎት ከሆነ ወይም ደግሞ የእኛን የውሂብ ጥበቃ ኃላፊ ማነጋገር ከፈለጉ፣ እባክዎን ያነጋግሩን (https://consumer.huawei.com/ uk/legal/privacy-questions)።
የዋና መስሪያ ቤታችን አድራሻ፦ Huawei Services (Hong Kong) Co., Limited, Room 03, 9/F, Tower 6, the Gateway, No. 9 Canton Road, Tsim Sha Tsui, Kowloon, ሆንግ ኮንግ. የምዝገባ ቁጥር 1451551።
እኛ የእርስዎን የግል ውሂብ በዚህ መግለጫ ወይም በሚመለከታቸው የውሂብ ጥበቃ ሕጎች መሰረት አናሰናዳም ብለው ካመኑ፣ በእርስዎ ሀገር/ክልል ውስጥ ያለ የውሂብ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር ወይም ሆንግ ኮንግ ውስጥ ያለ የግል ውሂብ የግላዊነት ኮሚሽነር ጋር ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ።
7. ይህን መግለጫ የምናድሰው እንዴት ነው?
ይህን መግለጫ በመጪዎቹ ጊዜያት ውስጥ ልናድሰው ስለምንችል በመተግበሪያ ቅንብሮች ውስጥ በየጊዜው የቅርብ ስሪቱን እንዲያጣሩ እናበረታታዎታለን። በዚህ መግለጫ ላይ ጉልህ ለውጦች በሚደረጉበት ጊዜ፣ በለውጡ ተፈጥሮ የሚወሰን ሆኖ በማሳወቂያ የንንግር ሳጥኖች፣ በተገፊ መልዕክቶች፣ በኢሜይሎች፣ እና በመሳሰሉት መንገዶች አስቀድመን እናሳውቅዎታለን።